Fana: At a Speed of Life!

ከ10 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት 10 ሺህ 633 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ 167 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር አስታወቀ፡፡

የግንባታ ወጪያቸው ወይም የኮንትራት መጠኑም 312 ነጥብ 27 ቢሊየን ብር መሆኑን አሥተዳደሩ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

በአንዳንድ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ በአሁኑ ወቅት የጸጥታ ችግር፣ የወሰን ማስከበር እና የማሽነሪ እጥረቶች እንደ ተግዳሮት የሚነሱ መሆናቸውን አብራርቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ ግንባታቸው ተጠናቅቀው ለአገልግሎት የሚበቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች እንዳሉ የጠቆመው የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር፤ በተለያዩ ምክንያቶች የተቋረጡ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን አመልክቷል።

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.