Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ የሥራ አፈጻጸም የሁለተኛ ቀን የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ሁለተኛ ቀን ግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት ቀጥሎ እየተካሄደ ነው፡፡

የግምገማ መድረኩ በአጠቃላይ ሀገራዊ ፖለቲካ ሁኔታ፣ ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ለማሳካትና በፓርቲና በመንግሥት ቅንጅት የሚሰሩ የንቅናቄ አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመድረኩም የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የዋና ጽ/ቤት የዘርፍ አመራሮች፣ የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የክልል የአደረጃጀትና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመርሐ-ግብሩ መሰረትም የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ በየደረጃው የተደረጉ ውይይቶች አፈጻጸም በተመለከተ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በሥራ እድል ፈጠራ፣ ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት የሚከናወኑ ስራዎችና ከተረጂነት ለመላቀቅ እየተሠሩ ያሉ ተግባራት ላይ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.