በጤናው ዘርፍ ሥር ነቀል ለውጥ መጥቷል- ዶ/ር መቅደስ ዳባ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጤናው ዘርፍ ባለፉት ጥቂት ዓመታት መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን በመተግበር ሥር ነቀል ለውጦችን ማምጣት ተችሏል ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሯ በጤናው ዘርፍ ቁልፍ የስትራቴጂክ አቅጣጫዎች አፈጻጸም ላይ ከሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም እንደ ሀገር ያጋጠሙ መሰናክሎችን በማለፍ የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት ተችሏል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
የተሻሻለው የጤና ፖሊሲ ጸድቆ ወደ ተግባር መገባቱን፣ የጤና አሥተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁን እና በዘርፉ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡
ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተገናኘ የወረርሽኞች መከሰትና፣ ከሰላምና ጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታትም ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡
በቀጣይ በተለይም የሀገር በቀል መድኃኒቶችና የክትባት ምርት አቅርቦትንና የዘርፉን ባለሙያዎች ዐቅም ለማሳደግ በትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡