Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴቶች የሚመራ በረራ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በሴቶች የሚመሩ 6 በረራዎችን እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የበረራ መርሐ ግብሩ ሴት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን ጭምር እንደሚያካትት ነው የተገለጸው።

በረራው በሴቶች የሚመራ መሆኑ ሴቶች በአቪዬሽን ዘርፉ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የሴቶች ቀን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እያከበረ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም በሴት አብራሪዎች እና የበረራ ቡድን ብቻ የተመራ በረራ ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.