Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ረመዳን መሐመድ አብደላ ጎክ ጋር ዛሬ በጁባ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳንን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከርና ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትብብርና የሕዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማሳደግ የበለጠ ተቀራርበው ለመስራት መስማማታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ጁባ መግባቱ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.