Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም ያጋጠመውን የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት መቀነስና መቆራረጥ ችግር ለመፍታት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቀይ ባህር ውስጥ በሚያልፍ ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ ዓለም አቀፍ ባህር ጠለቅ የኢንተርኔት መገናኛ መስመር ላይ ባጋጠመ መቋረጥ ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎቱ በሌሎች አማራጭ መስመሮች ብቻ እየሰራ በመሆኑ ሰሞኑን የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት መቀነስ እና መቆራረጥ እያጋጠመ እንደሚገኝ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።
አገልግሎቱን በፍጥነት ለማስቀጠል ከአገልግሎት አቅራቢዎቹ ጋር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን የገለፀው ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ መጠየቁን የኢትዮ ቴሌኮም መረጃ አመልክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.