የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎች የአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት በቅርቡ ግንባታው ተጠናቅቆ ለጎብኝዎች ክፍት የሆነውን የአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ ላይ ከጤና ተቋማት የተውጣጡ የጤናው ዘርፍ ሠራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞች እና ታዳጊዎች ተሳትፈዋል፡፡
ማዕከሉ ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የበለጠ እንድትነቃቃ እንደሚያደርጋት በዚሁ ወቅት ጎብኝዎቹ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ያለችበትን የዕድገት ደረጃ ያየንበት ነው ብለዋል፡፡
በቅድስት አባተ