Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የቆየው የብልጽግና ፓርቲ የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ፡፡

በመድረኩ፤ የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ውጤታማነትን በጥልቀት መገምገም መቻሉ ተገልጿል፡፡

የጠንካራ ፓርቲ፣ ጠንካራ መንግሥት እንዲሁም ጠንካራ ሀገር የመገንባት ግቦችን መሰረት በማድረግ በግማሽ ዓመቱ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸው ተጠቅሷል፡፡

ቀጣይነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባም መግባባት ላይ መደረሱን የፓርቲው መረጃ አመላክቷል፡፡

ባለፉት ወራት የፖለቲካ፣ የአደረጃጀት እና የሕዝብ ንቅናቄ ሥራዎች አፈጻጸም ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባም ተጠቁሟል።

ስኬቶችን ለማስቀጠል፣ ክፍቶችን ለመሙላት እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ነው የተገለጸው፡፡

በግምገማው በፓርቲው መዋቅር ግንባር ቀደም ተሣትፎ የሚከናወኑ የንቅናቄ አጀንዳዎች ላይ በመምከር የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል ተብሏል ።

በዚህም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ፣ ክኅሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ እንዲሁም ከተረጂነት መላቀቅ ሀገራዊ ግብን ለማሳካት የተሠሩ ውጤታማ ሥራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.