በዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የዓመታት ልፋቷን ዋጋ የተረከበችው ብርቱ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል ተማሪ የነበረችው ዚክራ ሰኢድ 3 ነጥብ 99 አማካይ ውጤት በማስመዘገብ የዩኒቨርሲቲውን የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልማለች፡፡
ከሽልማቱ በኋላ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሰጠችው አስተያየት፤ እየተከበረ በሚገኘው የሴቶች ቀን መመረቋ እና የወርቅ ሜዳሊያ መሸለሟ ደስታውን እጥፍ እንዳደረገላት ተናግራለች፡፡
ሴቶች እንደምንችል የኔ ውጤት ማሳያ ነው ያለችው ዚክራ፤ በቀጣይም ሀገሯን እና ሕዝቧን በተማረችበት ለማገልገል መዘጋጀቷን አረጋግጣለች፡፡
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪበተለያየ መርሐ-ግብር እና የትምህርት ዓይነት ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 320 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡