“መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ” መንፈሳዊ መርሐ-ግብር መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) “መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ” መንፈሳዊ መርሐ-ግብር በመስቀል ዐደባባይ መካሄድ ጀመሯል፡፡
መርሐ-ግብሩን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከቢሊ ግራሃም የወንጌል ማኅበር ጋር በመተባበር ነው፡፡
እየተካሄደ የሚገኘው መርሐ-ግብር፤ የጸሎት፣ የወንጌል ስብከት እና የዝማሬ ፕሮግራምን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ፤ መርሐ-ግብሩን በፀሎት አስጀምረውታል።
ከ1 ሺህ 600 በላይ አብያተ ክርስቲያናት ከቢሊ ግራሃም የወንጌል ማኅበር ጋር በመተባበር በመለኮታዊ ጉብኝት ላይ ተሳታፊ ናቸው ።
በመርሐ-ግብሩ ላይ በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
በበረከት ተካልኝ ፣ ሰለሞን በየነ እና ዘረዓያዕቆብ ያዕቆብ