Fana: At a Speed of Life!

አቶ አደም ፋራህ የሕዝቡን ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝባችንን ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች በስፋት እየተሠሩ ነው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አቶ አደም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ የፓርቲያችንን እሳቤዎች መሰረት በማድረግ በየአከባቢው የሕዝባችንን ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች በስፋት እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ለአብነትም በደቡብ ወሎ ዞን መንደርንና ቤተሠብን ማዕከል በማድረግ የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብርን ከወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በማስተሳሰር የተሠሩ ውጤታማ ሥራዎችን መጥቀስ ይቻላል ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.