Fana: At a Speed of Life!

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) የሃይማኖት አባቶች አንድነትን ለማጎልበት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ እንዲያጠናክሩ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ትናንት ምሽት ከመርቲ ወረዳ ኢማሞችና አቦምሳ ከተማ ነዋሪዎች ጋር አፍጥረዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የሃይማኖት አባቶች ለልማት፣ ለሕዝቦች አንድነት እና ለዘላቂ ሰላም መስፈን እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

ይህንን በጎ አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ መጠየቃቸውንም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የተያዘውን የጾም ወቅት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን በማስታወስና በመረዳዳት ማሳለፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.