በክልሉ በ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለሚገነቡ የቢሮ ሕንጻዎች የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ7 ማዕከላት በ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ ለሚገነቡ የቢሮ ሕንጻዎች የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) እና የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በተለያዩ ከተሞች የሚገነቡት የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት የከተሞችን እድገት በሚመጥን መልኩ እንደሚገነቡ ተጠቁሟል፡፡
በክልሉ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ መገለጹንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡