Fana: At a Speed of Life!

የአዳማ ስማርት ሲቲ ግንባታ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዳስቻለ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዳማ ከተማ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ የመንግሥትን አሠራር ሥርዓት ከማዘመን ባለፈ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ማስቻሉን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ።

በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የጋራ ጉባዔ የተሳተፉ የፌዴራልና የክልል መንግስት ኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ተቋማት ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የአዳማ ከተማን “ስማርት አዳማ ፕሮጀክት” ጎብኝተዋል፡፡

ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሠሩ ያሉ አካታችና ሁሉን አቀፍ የዲጂታላይዜሽን የልማት ኢኒሼቲቮች እያመጡ ያሉትን ለውጥ ለኅብረተሰቡ ከማስገንዘብ አንጻር የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ድርሻ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

የስማርት አዳማ ፕሮጀክት የከተማዋን የፀጥታ እና የመልካም አስተዳደር ችግር በእጅጉ ያሻሻለ መሆኑ ነው የተመላከተው፡፡

ሃላፊዎቹ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን የጎበኙ ሲሆን÷በዚህም የተቀናጀ የወተት ላሞች፣ የዓሣ፣ የዶሮ ዕርባታ፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት ሥራዎችን እንደተመለከቱ የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.