Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልልን ግብርና ማሸጋገር ሀገራዊ የብልጽግና ግብን ለማሳካት ትልቅ አቅም ነው  – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልልን ግብርና ማሸጋገር ሀገራዊ የብልጽግና ግባችንን ለማሳካት ትልቅ አቅም ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትሰስር ገጻቸው ÷ በዛሬው ዕለት የክልሉን ግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ በተዘጋጀው የአስር ዓመት የመነሻ ዕቅድ ላይ ከምሁራንና ከባለድርሻ አካላት ጋር መወያየታቸውን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በየክልሎች የሚገኙ የግብርና እምቅ ፀጋዎችን፣ ሀገር በቀል ፖሊሲና ሌሎች አቅሞችን ለመጠቀም ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ይህንን እምቅ ፀጋ ለይቶ ለልማት በማዋል እና የክልሉን የመልማት አቅም በማባዛት፣ ሀገርን ከድህነት ለማላቀቅ ትጋት፣ ትኩረትና መናበብን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

የአማራ ክልልን የ10 ዓመት መነሻ ዕቅድ ከሀገራዊ ግቦች ጋር በተናበበ መልኩ ለማስፈጸም የሥራ ባህልና የአመለካከት ለውጥ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው÷ ባለድርሻ አካላት በተነሳሽነትና በቁጭት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.