Fana: At a Speed of Life!

የአፋርና ሶማሌ ወንድማማች ህዝቦች የኢፍጣር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት በጅግጅጋ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር እና ሶማሌ ወንድማማች ሕዝቦች ታላቅ የጋራ የኢፍጣር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ይካሄዳል።
በመርሐ ግብሩ ለመሳተፍም የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ፣ የሰላም ሚኒስትር መሃመድ እድሪስ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል፡፡
እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና የፌደራል መንግስት ተቋማት ሃላፊዎች በመርሐ ግብሩ እንደሚታደሙ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.