ለአምባሳደር ምስጋኑ አርጋና ለአምባሳደር ሱለይማን ደደፎ የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ሹመት ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለአምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና ለአምባሳደር ሱለይማን ደደፎ የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ሹመት ሰጥተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ለሁለት የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ሹመት መስጠታቸውን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡