Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ኮሪያ በሕግ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፍትሕ ሚኒስትር ዴዔታ ተስፋዬ ዳባ በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጁንግ ካንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱ ሀገራት በሕግ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴዔታው የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዘርፍ ዋና ሃላፊነት በሀገሪቱ የሚፈፀሙ የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራና ክርክር በማድረግ ወንጀለኞችን ተጠያቂ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሀገራቱ ካላቸው ታሪካዊ ግንኙነት አንጻር ከንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት በተጨማሪ በሕግ ጉዳዮች፣ በመረጃና ልምድ ልውውጥ እንዲሁም ተቋማትን በማጠናከር በጋራ መስራት እንደሚገባቸው አንስተዋል፡፡

ጁንግ ካንግ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ መልካም ግንኙነት እንዳላቸው መናገራቸውን  የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሀገሪቱ ያሉ ኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርላቸው እና ተገቢውን የሕግ ጥበቃ እንዲያገኙ ማድረግ እንዲገባ አንስተዋል፡፡

ደብብ ኮሪያ በሕግ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት ያላት መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.