Fana: At a Speed of Life!

የአፋርና ሶማሌ ሕዝብን ወንድማማችነትና የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል – አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋርና ሶማሌ ሕዝብን ወንድማማችነትና የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ፡፡

የአፋር እና ሶማሌ ወንድም ሕዝብ ታላቅ የጋራ የኢፍጣር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል፡፡

አቶ አወል አርባ በመርሐ ግብሩ ባደረጉት ንግግር÷የሃሳብ ልዩነትን በውይይት እና በንግግር የመፍታት ልምድን ማዳበር እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ለልዩነቶች ወንበር መሳብ እስከተቻለ ድረስ የማይፈታ ችግር የለም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷የአፋር እና ሶማሌ ሕዝብን ወንድማማችነትና የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡

የኢፍጣር መርሐ ግብሩን ላዘጋጁት እና አቀባበል ላደረጉላቸው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ በሰመራ ከተማ ለሚደረገው የአፋርና ሶማሌ ወንድም ሕዝብ የጋራ ኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ ሁሉም እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር መሃመድ ኢድሪስ÷የሶማሌና የአፋር ክልል ሕዝብ ለልዩነትና ለግጭት ሳይሆን በጋራ ለመኖርና ለማደግ ብዙ ምክንያቶች እንዳሏቸው ጠቁመዋል፡፡

ወንድማማችነታቸውን ማጠናከር እንጂ በውይይት መፍታት በሚችሉ ጉዳዮች ለግጭት ሊዳረጉ እንደማይገባም ነው ያስገነዘቡት፡፡

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.