ሀገር አቀፉ የቁርዓን ሒፍዝ ውድድር ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ‘ቁርዓን – የእውቀትና የሰላም ምንጭ’ በሚል መሪ ሐሳብ በሁለቱም ጾታዎች ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፉ የቁርዓን ሒፍዝ ውድድር ተጠናቀቀ፡፡
በዚሁ መሠረት በወንዶች ከኦሮሚያ ክልል ቃሪዕ ሳላሀዲን አብዱረህማን እንዲሁም በሴቶች ከአማራ ክልል ቃሪዕ ሀፍሷ ከድር የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ሁለቱ አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው የመኪና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በዚሁ ውድድር በወንዶች ከአማራ ክልል ቃሪዕ ሙሀመድ አወል ሁለተኛ እንዲሁም ከሶማሌ ክልል ቃሪዕ አብዱሏሂ ዑስማን ሦስተኛ ሲወጡ፤ በሴቶች ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል ቃሪዕ ሱንዱስ አብዱረዛቅ ሁለተኛ እና ከሶማሌ ክልል ቃሪዕ አልያ ሙሀመድኑር ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
ለቀሪዎቹ ተወዳዳሪዎችም እንደየደረጃቸው የገንዘብ እና የሐጅ ጉዞ ሽልማት መዘጋጀቱ ተጠቅሷል፡፡
በሌላ በኩል 5ኛው ታላቁ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት በመስቀል ዐደባባይ ተካሂዷል፡፡