Fana: At a Speed of Life!

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከብራዚል አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ዣንዲር ፌሔይራ ዶስ ሳንቶስ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸውም በግብርና ልማት ትብብር በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችና በቀጣይ የሚከናወኑ ሥራዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአፈር ለምነትና ጤንነት አጠባበቅ፣ የግብርና ሜካናይዜሽን እና የግብርና ወጪ ንግድ ሥራዎች በዋናነት ትኩረት አድርጋው የተወያዩባቸው ጉዳዮች መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡

በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ወደፊት በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.