ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢንዱስትሪ ዘርፍን በተመለከተ የሰጡት ምላሽና ማብራሪያ:-
👉 በኢንዱስትሪው ዘርፍ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ መንግስት ጣልቃ በመግባት የኢኮኖሚ መሻሻያ አድርጓል፤ በዚህም ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል፣
👉 የሀይል አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በተከናወኑ ተግባራት በዘርፍ ኢነርጂ 100 ፐርሰንት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፣ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር በኢንዱስትሪው ዘርፍ 50 በመቶ የሀይል አቅርቦት ጭማሪ ተደርጓል፣
👉 ከግብዓት ጋር እንዲሁም ከኢንዱስትሪ መሬት አቅርቦት ጋር በተያያዘ መንግስት በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፣
👉 ኢትዮጵያ 100 በመቶ የብረት ምርት በሀገር ውስጥ ማምረት ጀምራለች፤ በቀጣይም የብረት ምርት ግብዓቶችን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ለማድረግ እየተሰራ ነው፣
👉 የሲሚንቶ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በተከናወኑ ተግባራት ፋብሪካዎችን ማስፋፋት ተችሏል፤ በዚህም ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ የሚያስችል ሲሚንቶ ማምረት ተችሏል፣
👉 በተጨማሪም በሴራሚክስ፣ ግራናይት፣ ማርብል፣ የቴክስታይል እና የምግብ ማቀነባበሪያ ምርቶችን የማምረት ስራዎች በስፋት እየተሰሩ ይገኛሉ፣
👉 በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ፋብሪካዎች የማምረት አቅማቸው 61 በመቶ ደርሷል፣ 55 አዳዲስ ግዙፍ ፋብሪካዎች ወደ ስራ ገብተዋል፤ በዚህም በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በኢንዱስትሪው ዘርፍ የታቀደውን ግብ ማሳካት የሚያስችል አቅም ተገንብቷል፡፡