ኢትዮጵያ እና ባርባዶስ በትብብር በሚሠሩበት ጉዳይ ላይ መከሩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በኬንያ የባርባዶስ ከፍተኛ ኮሚሽነር እና በናይሮቢ የተባበሩት መንግሥታት ቋሚ ተወካይ ከሆኑት ዊሊያም አሌክሳንደር ማክዶናልድ ጋር ተወያዩ፡፡
በዚሁ ወቅትም በትብብር መሥራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል ሲሉ ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ውይይቱ የሰው ኃይል ልማትና ስምሪት ዝርዝር አፈፃፀም ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸው፤ ወደ ተግባር የሚሸጋገርበትን ውጤታማ ምክክር አድርገናል ብለዋል፡፡
ዊሊያም አሌክሳንደር ማክዶናልድ በትብብር ለመሥራት ላሳዩት ቁርጠኝነትም ሚኒስትሯ አመሥግነዋል፡፡