የቲቢ በሽታን ለመከላከል በትኩረት እየተሠራ ነው- ጤና ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁሉ አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና ችግር የሆነውን የቲቢ በሽታ ለመከላከልና ለመግታት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ደረጄ ዱጉማ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
19 ኛው ዓመታዊ የቲቢ ምርምር ጉባዔ እና የ2017 ዓ.ም የዓለም የቲቢ ቀን በአርባምንጭ እየተከበረ ነው፡፡
ሚኒስትር ዴዔታው በዚሁ ወቅት፤ የሕብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግና በሽታውን ለመግታት ከ100 በላይ ጥናትና ምርምሮች መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ከነዚህ ጥናትና ምርምሮች መካከልም 20ዎቹ ተመርጠው በመድረኩ እየቀረቡ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከዚህ ቀደም የቲቢ በሽታን መርምሮ ለማሳወቅ ሦስት ቀናት እንደሚፈጅ አውስተው፤ አሁን ላይ በደቂቃዎች ማሳወቅ የሚችል 1 ሺህ ማሽን ለ140 በላይ ተቋማት ተደራሽ መደረጉን ተናግረዋል።