Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ቤላሩስ የኢንቨስትመንት አጋርነታቸውን በይበልጥ ለማሳደግ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ከቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ሪዚሄንኮቭ ጋር በሁለትዮሽ የትብብር ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች ላይ ተወያዩ፡፡

በዚሁ ወቅትም በግብርና እና ሜካናይዜሽን እንዲሁም በኢነርጂ ዘርፎች የጋራ ትብብር መፍጠር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ መረጃ አመላክቷል፡፡

ሁለቱም ወገኖች የኢንቨስትመንት አጋርነትን ለማጎልበት እና ለሀገራቱ ዘላቂ ልማት ብሎም ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን የሚደግፉ የጋራ ተግባራትን ለማከናወን ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.