Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ መንግስት የሜዳሊያ ሽልማት ተበረከተላቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ላገለገሉት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ‘ጁን 27 ኦፊሰር ዳንስ ላሬድ’ የተባለውን የሀገሪቱ የዲፕሎማሲ የክብር ሜዳሊያ ከጅቡቲ መንግስት ተቀብለዋል፡፡

አምባሳደር ብርሃኑ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናክር ላሳዩት ቤተሰባዊ ድጋፍ ከጂቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

የዲፕሎማሲ የክብር ሜዳሊያ የሆነውን የጁን 27 ኦፊሰር ዳንስ ላሬድ ናሽናል ሜዳልያ ሽልማት ከጅቡቲ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ካሚል መሀመድ መቀበላቸውን እና በሽልማቱ መደሰታቸውን የገለጹት አምባሳደር ብርሃኑ፤ ጅቡቲ ሁለተኛ ሀገሬ ናት ብለዋል።

የኢትዮጵያና የጅቡቲ ግንኙነት በጋራ ህዝቦች ላይ የተመሠረተ ጠንካራ ወዳጅነት እና የዘመናት ወንድማማችነት ያለን ህዝቦች ነን ሲሉ ገልጸዋል።

ለቀጣናው ተምሳሌት የሆነው የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ  ትስስር በአህጉራዊ እና አፍሪካዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚቀጥልም ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በጅቡቲ ቆይታቸው ትብብር ላደረጉላቸው ተቋማት እና ግለሰቦች ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.