ክሪስታል ፓላስ አስቶን ቪላን በማሸነፍ ለኤፍ ኤ ካፕ ፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ የኤፍ ኤ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ አስቶን ቪላን 3 ለ 0 በማሸነፍ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
ምሽት 1፡15 በዌንብሌይ በተደረገው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ የፓላስን የማሸነፊያ ግቦች ኤቤርቺ ኤዜ እና ኢስማኤላ ሳር (2) አስቆጥረዋል፡፡
በሌላ የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር ማንቸስተር ሲቲ ከኖቲንግሃም ፎረስት በነገው ዕለት የሚጫወቱ ሲሆን፥ ክሪስታል ፓላስ ከሁለቱ ክለቦች አሸናፊ ጋር ለፍጻሜ ይፋለማል፡፡