አዳማ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር የተገናኙት አዳማ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ፤ ነቢል ኑሪ ለአዳማ ከተማ እንዲሁም ዳዋ ሁጤሳ ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡