Fana: At a Speed of Life!

በዓለም የሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ለተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ፍሎሪዳ በተካሄደው 46ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ዛሬ ጠዋት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገው የአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት ስለሺ ስህን፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) እና ሌሎችም አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በመድረኩ በሶስት የወርቅ፣ ሁለት የብር እና ሁለት የነሃስ በአጠቃላይ 7 ሜዳሊያዎችን ያገኘች ሲሆን፥ ኬንያን በመከተል ከዓለም 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

 

በትዝታ ወንድሙ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.