የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ማዳበሪያን ቀላቅሎ መጠቀም ምርታማነት እንደሚያሳድግ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቀጣዩ የመኸር ወቅት የተፈጥሮ ማዳበሪያን ከሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ጋር ቀላቅሎ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ ግብርና ሚኒስቴር አስገንዝቧል፡፡
በሚኒስቴሩ የአፈር ሃብት ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሊሬ አብዬ እንዳሉት፤ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ላይ የተሠራው ሥራ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር ንጥረ ነገር ያጡ መሬቶችን ወደ ቀድሞ ለምነታቸው መልሷል፡፡
የተፈጥሮ አፈር ማዳበሪያን ከኬሚካል ማዳበሪያ ጋር በጋራ መጠቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ የመጣውን የአፈር ለምነት ወደቀደመ አቋሙ መመለስ እንደሚችልም አረጋግጠዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተቋማቸው ቨርኒ ኮምፖስትን በመጠቀም ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል፡፡
የተፈጥሮ ማዳበሪያ፤ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ጨምሮ በርካታ ሰብሎች ላይ ምርትና ምርታማነትን ከመጨመር አንጻር አበርክቶው ከፍ ያለ በመሆኑ አርሶ አደሩ እንዲጠቀመው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በፀጋዬ ንጉሥ