ባህር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ቀን 10:00 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ሙጂብ ቃሲም እና ሔኖክ ይበልጣል ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
ኢትዮጵያ መድህን ከሽንፈት ያልታደገውን ግብ ረመዳን የሱፍ አስቆጥሯል።