Fana: At a Speed of Life!

ከኢራን ጋር የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበናል አሉ ፕሬዚዳንት ትራምፕ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከኢራን ጋር የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበናል ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ÷ ኢራን ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረበቸውን የኒውክሌር ድርድር ነጥብ በአዎንታ እንደተመለከተችው አንስተዋል፡፡

የኒውክሌር ስምምነት ሒደቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው÷በሚቀጥሉት ቀናት ኢራን የድርድር ሃሳቡን ልትቀብል እንደምትችል አመልክተዋል፡፡

ኢራን የቀጣናው ሃያል ሀገር ለመሆን የምታደርግውን ጥረት እንደግፋለን ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ÷ በአንጻሩ ቴህራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንድትታጠቅ አንፈቅድም ብለዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል ዘላቂ ሰላምን ማስፈን የሚያስችል የኒውክሌር ስምምነት እንዲፈረም አሜሪካ የድርድር ሒደቱን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

አራተኛው ዙር የአሜሪካ እና ኢራን ቀጥተኛ ያልሆነ የኒውክሌር ውይይት በሳለፍነው እሑድ በኦማን መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር አስታውቋል÷ከአሜሪካ ጋር የተደረገው ፈታኝ የኒውክሌር ውይይት ጠቃሚ ሃሳቦች የተገኙበት እንደነበር አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት እየተደረገ ያለው የኒውክሌር ድርድር የሚጠናቀቅ ከሆነ የኢራን ዩራኒዬም የማበልጸግ መጠን የሚገደብ ሲሆን÷በምላሹ አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እንደምታነሳ መገለጹን አይራን ዋየር ኒውስ ዘግቧል፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.