Fana: At a Speed of Life!

ሸገር ከተማ የመላው ኦሮሚያ ስፖርት ውድድር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአምቦ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የመላው ኦሮሚያ የስፖርቶች ውድድር ዛሬ ተጠናቅቋል።

በውድድሩ ከ8 ሺህ በላይ ስፖርተኞች በ20 የስፖርት ዓይነቶች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አወሉ አብዲ፤ ውድድሩ በርካታ ማኅበረሰቦችን በአንድ አሰባስቦ የሚደረግ ስለሆነ ጠንካራ ትስስር ይፈጥራል ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ ደሳለኝ ጥላሁን በበኩላቸው፤ የውድድሩን ውጤታማነት ተናግረዋል፡፡

የሸገር ከተማም በ220 ሜዳልያዎች እና በ28 ዋንጫዎች የአጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።

ቀጣዩ የመላው ኦሮሚያ ስፖርታዊ ውድድር በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

በዳዊት መሐሪ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.