ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ30ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ብቸኛ ግብ ማይክል ኪፕሩቪል በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሁለተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ ወላይታ ድቻ በበኩሉ ሁለተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በ43 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወላይታ ድቻ በ41 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡