ኢትዮጵያ መድን መቐለ 70 እንደርታን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን መቐለ 70 እንደርታን 1 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ አቡበከር ሳኒ የኢትዮጵያ መድንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡
ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ መድን ነጥቡን ወደ 60 ከፍ በማድረግ ለዋንጫ የሚያደርገውን ግስጋሴ ሲያጠናክር፤ መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ሌላኛ መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ በሀቢብ ከማል ብቸኛ ጎል አርባ ምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡