ሸገር ከተማ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አስቀድሞ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጉን ያረጋገጠው ሸገር ከተማ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ አሸናፊ ሆኗል፡፡
የከፍተኛ ሊጉ የ26ኛ ሳምንት እና የውድድር ዓመቱ የማጠቃለያ መርሐ ግብሮች የተደረጉ ሲሆን÷ ቀን 8 ሰዓት ላይ ሸገር ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና 3 አቻ ተለያይተዋል።
ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ 64 ነጥብ የሰበሰበው ሸገር የሴቶች ቡድን ውድድሩን በበላይነት በማጠናቀቅ ሻምፒዮን መሆን ችሏል፡፡
ይርጋጨፌ ቡና ሴቶች ቡድን 54 ነጥብ በመያዝ 2ኛ ደረጃን ሲይዝ÷ኢትዮጵያ ስፓርት አካዳሚ ሴቶች ቡድን ደግሞ በ46 ነጥብ 3ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቅቋል፡፡
የ2017 የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ሲጠናቀቅ ሸገር ከተማ እና ይርጋጨፌ ቡና ሴቶች ቡድን ፕሪሚየር ሊጉን ሲቀላቀሉ ፤ሀዲያ ሆሳዕና እና ኡራ አፋፍሪ ወደታችኛው የሊግ እርከን ወርደዋል።
በሌዊ በለጠ