Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያና ዩክሬን ከፍተኛ የተባለውን የጦር እስረኞች ልውውጥ አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያና ዩክሬን በሶስት ቀናት ውስጥ ከፍተኛ የተባለውን የጦር እስረኞች ልውውጥ ማከናወናቸው ተገለጸ፡፡

የጦር እስረኞች ልውውጡ በቱርክ ኢስታንቡል በተደረገው የሁለቱ ሀገራት የቀጥታ ውይይት እና ድርድር በኋላ በተደረሰው ስምምነት የተፈጸመ መሆኑ ተነግሯል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ በዛሬው ዕለትኪየቭ 303 የዩክሬን ወታደሮች እና ሲቪሎች ስትለቅ ሞስኮም ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸውን የጦር እስረኞችን ለዩክሬን አስረክባለች፡፡

ከሩሲያ የተለቀቁት የጦር እስረኞች አሁን ላይ ቤላሩሰ የሚገኙ ሲሆን በቀጣይ ቀናት በሩሲያ መከላከያ ውስጥ ወደሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እና መልሶ ማቋቋሚያ ስፍራዎች በመግባት የጤና እና የስነ-ልቦና ህክምና እንደሚያገኙ ተመላክቷል፡፡

እንደ አርቲ ዘገባ ሩሲያ እና ዩክሬን 1 ሺህ የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ የደረሱትን የኢስታንቡል ስምምነት በፈረንጆቹ 2025 ከግንቦት 23 እስከ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ አድርገዋል፡፡

ባለፈው አርብ በተጀመረው የእስረኞች ልውውጥ በሁለት ቀናት ብቻ ከ697 በላይ የሲቪል እና የወታደር የጦር እስረኞችን የተለዋወጡ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ 303 የጦር እስረኞችን ተለዋውጠዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.