Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር  ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬ የብሔራዊ ቤተ መንግሥት መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሀገር ግንባታ ተገቢውን አስተዋጽዖ እንድታበረክት መንግሥት የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚወጣ መግለፃቸውንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

አዲስ ለተመደቡት ብጹአን አባቶች መልካም የሥራ ዘመን ተመኝቻለሁም ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.