Fana: At a Speed of Life!

የአፈር ማዳበሪያ የአቅርቦት ስራን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘዋወር የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፈር ማዳበሪያ ተደራሽነትን ለማሳደግ የአቅርቦት ስራውን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘዋወር የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ይገኛል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት÷ የአፈር ማዳበሪያ ተደራሽነትን ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

በተለይም የአቅርቦት ስራውን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘዋወር የህግ ማዕቀፎች እየተዘጋጁ መሆናቸውን አንስተው÷ የግብርና እንቅስቃሴ እያደገ በመምጣቱ የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት መጨመሩን ተናግረዋል።

በሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎች ላይ ጥገኛ ከመሆን ይልቅ የተፈጥሮ ማዳበሪያዎችን የማዘጋጀት እና የመጠቀም ባህላችን ሊያድግ ይገባል ያሉት ሶፊያ (ዶ/ር)÷ ግብርናውን ለማሳደግ ቴክኖሎጂን በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል ብለዋል።

የሜካናይዜሽን መሳሪያዎች ተደራሽነት እያደገ መምጣቱን ጠቁመው÷ መሳሪያዎችን ከውጭ በማስመጣት ብቻ ስኬታማ መሆን እንደማይቻልና ባለሃብቶች ከፈጠራ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር በዘርፉ ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ አድርገዋል።

በተጨማሪም ለአርሶ አደሮች በምርምር ተቋማት እጅ የሚገኙ የሀገር ውስጥ ዝርያ ያላቸውን ምርጥ ዘሮችን ጨምሮ ከውጪ የሚመጡ አዝዕርቶች የማባዛት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.