Fana: At a Speed of Life!

የፌስቱላ ተጠቂዎችን ለማገዝ የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በወሊድ ወቅት የሚከሰት የፌስቱላ ተጠቂዎችን ለማገዝ የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያው በወሊድ ወቅት የሚከሰት ፌስቱላን በተመለከተ አጋርነትን ለማጠናከርና እየተሰሩ ያሉ ወሳኝ ስራዎችን ለማገዝ ይረዳል ነው የተባለው፡፡

‘ትኩረት የተነፈጋቸው የፌስቱላ ተጠቂዎችን ህይወት ለመታደግ’ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ የሚገኘው የገቢ ማሰባሰቢያው ከዘንድሮው ዓለም አቀፍ በወሊድ ወቅት የሚከሰት ፌስቱላን የማቆም ቀን ጋር በማያያዝ የተዘጋጀ ነው።

የሚገኘው ገቢ በወሊድ ወቅት በሚከሰት ፌስቱላ እና የማህፀን መውረድ ተጠቂ ሴቶችን የመለየት፣ ቀዶ ህክምና፣ አጠቃላይ የድህረ ቀዶ ህክምና ክትትል አገልግሎትን ጨምሮ የተሀድሶ እና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ በማድረግ ተጠቂዎች ማህበረሰቡን ተመልሰው እንዲቀላቀሉ ድጋፍ ያደርጋል።

የገቢ ማሰባሰቢያው በጤና ሚኒስቴር፣ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በሀምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ እና በተባበሩት መንግስታት የስነ ሕዝብ ፈንድ ትብብር መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡

በኢትዮጵያ በየዓመቱ 9 ሺህ ሴቶች በወሊድ ወቅት በሚከሰት ፌስቱላ የሚጠቁ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺህ 500 የሚሆኑት ብቻ በሀገሪቱ በሚገኙ ዘጠኝ የፌስቱላ ህክምና ተቋማት ህክምና እንደሚያገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.