የዛሬን ችግር በውይይት መፍታት የሁላችንም ድርሻ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል ተቋማትና ማኅበራት አጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ተሳታፊዎች በጋራ የሐሳብ ተዋጽኦ የጸናች ሀገርን ለትውልድ ለማስረከብ የዛሬን ችግር በውይይት መፍታት የሁላችንም ድርሻ ነው አሉ።
ለዚህም የሚፈለገውን ድርሻ ለመወጣት በንቃት እየተሳተፍን ነው ብለዋል።
የነበሩ ችግሮችን በጋራ የውይይት መድረክ መፍታት እንዲቻልና መሰል መድረኮች እንዲፈጠሩ ለዘመናት ሲጠየቅ መቆየቱን የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
ዛሬ የተገኘውን እድል በመጠቀም ለነገ በሐሳብ መሰረት ላይ የጸናች ሀገር ለማቆም ከሁላችንም የሚጠበቀውን ኃላፊነት እየተወጣን ነው ሲሉም ተወያዮቹ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
ከትላንት ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የፌደራል ተቋማት እና ማህበራት አጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ተሳታፊዎች በሚዋጡ ሐሳቦች ላይም የጋራ አቋም መያዝ የሚያስችል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።
በይስማው አደራው