Fana: At a Speed of Life!

የተቋማትና ማህበራት ተወካዮች የየቡድን አጀንዳዎችን ለጠቅላላ ተሳታፊዎች አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል ተቋማትና ማህበራት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ተሳታፊዎች የየቡድን አጀንዳዎችን በሰብሳቢዎች አማካይነት ለጠቅላላ ተሳታፊዎች አቅርበዋል።

የቀረቡት ዝርዝር አጀንዳዎች ከሰባት ቡድኖች በሚመረጡ ወኪሎቻቸው አማካይነት እጅግ መሰረታዊ የሆኑ ነጥቦች ተለይተው በአንድ ሰነድ መልክ ይዘጋጃሉ።

የተደራጁት አጀንዳዎችም በነገው ዕለት ለተሳታፊዎች ከቀረቡ በኋላ የፌደራል ተቋማትና ማኅበራት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

አጀንዳቸውን ያቀረቡት ቡድኖች የሃይማኖት እና የዴሞክራሲ ተቋማት ወኪሎች፣ የመንግስት አካላት፣ መገናኛ ብዙኃንና የማህበረሰብ አንቂዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፀጥታና ደህንነት አካላት፣ የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች እና ልዩ ልዩ ማህበራትና ተቋማት ናቸው።

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.