በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ሩዝን በስፋት ለማምረት ዝግጅት እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ሩዝን በስፋት ለማምረት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ በሪሶ ፈይሳ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ በ2017/18 መኸር እርሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በሩዝ ሰብል ይሸፈናል።
በመኸር ወቅት በሩዝ ሰብል የሚሸፈነው መሬት መለየቱን ገልጸው÷ ከዚህም ከ40 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል ብለዋል።
በተመሳሳይ በአማራ ክልል ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሩዝ ሰብል ለማልማት የማሳ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በዚህም በሄክታር 55 ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
በዙፋን ካሳሁን