Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ እና ሐረሪ ክልሎች ከ202 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተዘጋጅተዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ እና ሐረሪ ክልሎች ከ202 ሺህ 200 በላይ ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተዘጋጅተዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከ200 ሺህ በላይ ተማሪዎች በወረቀት እና በበይነመረብ ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አማካሪ ኤፍሬም ተሰማ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በሐረሪ ክልል ከ2 ሺህ 200 በላይ ተማሪዎች ለፈተና መዘጋጀታቸውን የገለጹት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ለቶ ናቸው፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከ28 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንዲሁም በሐረሪ ክልል ከ 1 ሺህ 900 በላይ ተማሪዎች በበይነ መረብ ለመፈተን ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ለተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

በስንታየሁ አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.