Fana: At a Speed of Life!

በክልሎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለማቋቋም ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ እና ሐረሪ ክልሎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማቋቋም ዝግጅት እያደረግን ነው አሉ፡፡

በፌደራል ደረጃ ወደ ሥራ የገባው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋም በክልሎች እንዲጀመር አቅጣጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሠረት የሲዳማ ክልል ማዕከሉን ለማቋቋም ዝግጅት እያረገ መሆኑን የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አሰፋ ጉራቻ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል፡፡

ለዚሁ ማዕከል የሚሆን ሥፍራም በሐዋሳ ከተማ መለየቱን ነው ኃላፊው ያስታወቁት፡፡

በሐረሪ ክልልም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለማቋቋም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ያስረዱት የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዚነት ዩሱፍ፤ ለዚሁ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ መለየቱን አረጋግጠዋል፡፡

በሚቀጥለው ዓመት አገልግሎቱን ለሕዝብ ክፍት ለማድረግ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም ኃላፊዎቹ አረጋግጠዋል፡፡

ማዕከሎቹ አገልግሎቶችን በዲጂታል ሥርዓት አስተሳስረው ወደ ሥራ ሲገቡ በተለያዩ ተቋማት ይሰጡ የነበሩትን አገልግሎቶች በተደራጀ መልኩ በማቅረብ የባለጉዳዮችን መጉላላት እንደሚቀርፉም አስረድተዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.