Fana: At a Speed of Life!

የአርሶ አደሮች የመኖሪያ መንደር ግንባታ ሲጠናቀቅ የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘዬ የሚቀይሩ ናቸው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአርሶ አደሮች የመኖሪያ መንደር ግንባታ ሲጠናቀቅ የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘዬ የሚቀይሩ እና ጤናማ ህይወትን የሚያላብሱት ናቸው አሉ፤

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አራተኛውን እና የክረምት በጎ ፍቃድ ስራ አካል የሆነውን የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ሁልባረግ ወረዳ ወራበት ሻማ ቀበሌ ሞዴል የአርሶ አደሮች የመኖሪያ መንደር ግንባታ አስጀምረዋል።

እነዚህ መኖሪያዎች ተገንብተው ሲጠናቀቁ የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘዬ የሚቀይሩ እና ጤናማ ህይወትን የሚያላብሱት መሆናቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዞኑ በነበራቸው ቆይታ የግሉ ዘርፍ በአግሮ ኢንዱስትሪ ላይ ያለውን ተሳትፎ መመልከታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

እንደማሳያ አቶት የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪን ተዘዋውረን ተመልክተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ እንዲህ ያሉት ስራዎች በሌማት ትሩፋት ውጤት ለማስመዝገብ የተጀመረውን ተግባር ከግብ ለማድረስ በጎ ጅምሮች በመሆናቸው ሊበረታቱ ይገባል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.