Fana: At a Speed of Life!

መምህራን የተሻለች ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ያላቸው ሚና የላቀ ነው – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የተሻለች ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት የመምህራን ሚና የላቀ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
“ትውልድ በመምህራን ይቀረጻል ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ ሐሳብ በክልሉ እየተካሄደ የቆየው የመምህራን ውይይት የማጠቃለያ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ባለፉት ዓመታት የትምህርት ስብራቱን ለመጠገን የሚያስችሉ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡
የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ፣ የትምህርት ግብዓት ማሟላትና የመምህራንን አቅም የማሳደግ ሥራዎች ተከናውነው ተጨባጭ ለውጦች መጥተዋል ብለዋል።
የትምህርት ስብራት ለመጠገን የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በዚህም የዘርፉ ዋና ተዋናይ የሆኑት መምህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
መምህራን በጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ያላቸውን ሚና በመረዳት የግል የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው አካላት አጀንዳ ባለመጠለፍ ለሀገርና ህዝብ ያላቸውን ውግንና ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
መምህራን ለሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት ያላቸው አስተዋጽዖ ጉልህ በመሆኑ ሙያዊ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩም ተጠይቋል፡፡
በፍሬው ዓለማየሁ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.