Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያለፉት ሰባት ዓመታት የመንግሥት ሥራ እንቅስቃሴ እና የቀጣይ አቅጣጫዎች አስመልክቶ ባደረጉት ልዩ ባለ አራት ክፍል ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያ ክፍል ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

👉 ኢትዮጵያዊነት የጋራ ዕጣ ፋንታ ነው።

👉 የሚያሰባስበን እና እንደቤተሰብ እንድንታይ የሚያደርገን ትርክት ያስፈልጋል።

👉 ብሔራዊ ጥቅም ማለት በትውልድ ቅብብሎሽ መካከል የሚጸናና ኢትዮጵያዊነትን የሚያቆይ ሥራ ነው።

👉 ብሔራዊ ጥቅም ስንል ከእኛ ከግል ፍላጎት እና መሻት የተሻገረ ማለት ነው።

👉 በአንድ ትውልድ፣ በአንድ ቤተሰብ፣ በአንድ ቡድን ሀገር ተሠርቶ አያልቅም፤ ሀገር የቅብብሎሽ ውጤት ነው።

👉 ኢትዮጵያዊነት ሲመቸን፣ ሲደላን፣ ጥቅም ስናገኝበት የምናዜመው የምናወድሰው ሲከፋን ሳይመቸን ሲቀር ህልሞቻችን ሲጨነጋገፉ የምንተወው የወረት ጉዳይ አይደለም።

👉 ኢትዮጵያዊነት ኩልል ብሎ የሚፈስ ጅረት ነው። አንዳንዴ ዘንቦ ሊደፈርስ ይችላል ነገር ግን ሰክኖ ይጠራል።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.