Fana: At a Speed of Life!

5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ሰኔ 7 ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የፊታችን ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ይጀመራል፡፡

በውድድሩ የምዕራፍ 17፣ 18 እና 19 አሸናፊዎች እንዲሁም ምርጥ አራት ተሰናባቾች ዳግም ተመልሰው በአጠቃላይ 16 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ፡፡

ለአሸናፊዎች አጠቃላይ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን ÷ ዋንጫ እና የአዲስ ወጥ ሙዚቃ ሽልማትም ተዘጋጅቷል፡፡

የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት በሚያደርገው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖራል፡፡

በ13ኛው ሳምንት አራት ምርጥ ተወዳዳሪዎች ለፍጻሜው የሚፋለሙ ሲሆን÷ 5ኛው የፋና ላምሮት አሸናፊዎች አሸናፊ ኮከብ ይለይበታል።

ውድድሩ በየሳምንቱ በተለያየ ሙያ ውስጥ ባሉ ተጋባዥ ዳኞች ጭምር ይደምቃል።

የመጀመሪያዋ የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ መቅደስ ግርማ ስትሆን ÷ አህመድ ሁሴን ፣ ያለምወርቅ ጀምበሩ እና ባምላክ ቢያድግልኝ ደግሞ በቅደም ተከተል 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛውን ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም የሚጀመረውን 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ደማቅ ውድድር በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሁሉም አማራጮች በቀጥታ ሥርጭት ይተላለፋል።

ይጠብቁን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.