ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአንበሳ ጋራዥ-ጃክሮስ-ጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ሥራ ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር በመሆን የተጠናቀቀውን የአንበሳ ጋራዥ-ጃክሮስ-ጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ሥራ ዛሬ ተመልክተዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራው 8 ኪሎሜትር የእግረኛ መንገድ፣ 4 ኪሎሜትር የብስክሌት መጋለቢያ፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ሱቆች፣ በመላው ከተማዋ እንደተገነቡት ያሉ የተለያዩ ዘመናዊ የሕዝብ መገልገያዎች ግንባታን ማካተቱ ተገልጿል።
ይህ ለውጥ በከፍተኛ የፍሰት መጨናነቅ በሚታወቀው ከባቢ በእጅጉ ሲፈለግ የነበረውን የፍሰት መሻሻል እና የኑሮ ደረጃ ከፍታ የሰጠ ሆኗል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።